መቼም፣ የትም እንዳይደገም

የአርታኢው መልእክት

የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማኅበር አዲስ የአመራር ቦርድ ከተመረጠ አንድ ዓመት ሊሞላው ነው። የቦርዱ አባላት ባደረጉት ተከታታይ ጥረት በርካታ የማኅበሩን የአሠራር ሕጸጾች በመለየት የማስተካከያ ርምጃዎች ወሰደዋል፣ እናም ሙዚየሙ ከነበረበት ውስብስብ ችግሮች በአብዛኛው አላቀውታል። ከዚኽም በተጨማሪ ማኅበሩ እንደተቋም እንዲንቀሳቀስ አስፈላጊ መዋቅር ዘርግተዋል። ከነዚህ መዋቅሮች አንዱ የአርትዖት ኮሚቴ ነው። ለመተርጎም እንደ ዋነኛ መሣሪያ ከሚያገለግሉት ነገሮች መካከል አንዱ መጽሔት ነው። በነገራችን ላይ፣ ማኅበሩ በተቋቋመበት ጥቂት ዓመታት ቋሚ የአርትዖት ኮሚቴ ነበረው። ኾኖም በቦርድ አባላት መቀያየር የተነሳ ኮሚቴው በመፍረሱ የመጽሔት ዝግጅቱ ባለቤት አልባ ሆኖ ቆይቷል። ይህን ያዩ ጥቂት አባላት በግል ተነሳሽነት ስከ 2009 ዓም ድረስ ለኅትመት ከኮሚቴው ዋነኛ ተግባራት አንዱ (በመመሪያው እንደተጠቀ ሰው) እንዲበቃ ሲያደርጉት ነበር። ይኽ በዚህ እንዳለ ነው አሁን ያለው አዲሱ የማኅበሩ ቦርድ የማኅበሩን መሪ-ቃል (Motto) ማለትም “መቼም፣ የትም እንዳይደገም” የሚለውን የሚያራ ምዱ ጽሑፎችን ማበረታታት፤ ማደራጀት፤ ማሳተምና ለማሠራ ጨት ነው። ይኽን በተግባር ያቋቋመው
የአርትዖት ኮሚቴ መጽሔቱን ለማስቀጠል ኃላፊነቱን ወስዶ በእንቅስቃሴ ላይ ነው። ይኽን ተከትሎ፣ የአርትዖት ኮሚቴው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ (ከበጀት አንጻር) በወርኃ ሚያዚያ የሚወጣ መጽሔት ለማዘጋጀት አቅዶ ነበር። ኾኖም የሙዚየማችን እንቅስቃሴ እያደገ በመምጣቱ እና በዓመት ኹለት ጊዜ ለማውጣት ኹኔታው ስለፈቀደ ከሚያዚያው መጽሔት በተጨማሪ ይኽን መለስተኛ
ይዘቶችና ገጾች ያሉትን መጽሔት ለኅትመት ለማብቃት ችሏል። በመጽሔታችን የሚወጡ ጽሑፎች ይዘት በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ “መቼም፣ የትም እንዳይደገም” በሚለው መሪ ቃል ዙሪያ ሚያጠነጥኑ እንዲሆኑ ቢፈለግም፣ 1ኛ ጽሑፍ አቅራቢዎች ኹሉ በዚያ ዙሪያ ለዝግጅት ክፍሉ ባለመላካቸው 2ኛ በተጠቀሰው መቸት ዙሪያ ብቻ ቢወጣ አሰልቺ ሊኾን ስለሚችልና የአንባቢን
ቁጥርና ዓይነት ስለሚወስነው፣ በመጠኑም ቢሆን ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ጽሑፎች መቅረባቸው አልቀረም። ስለዚኽ፣ አንባቢያን የመጽሔቱን ይዘቶች ከዚያ መንፈስ አንጻር እንድትረዱት በትሕትና እንጠይቃለን።


መቼም፣ የትም እንዳይደገም‼

የቦርዱ መልእክት

በሀገራችን ታሪክ የ-1966 አብዮት፣ ከኛም አልፎ በዓለም ታሪክ ውስጥ የሚወሳ ቢኾንም፣ በውጤት ደረጃ በሕዝባችን ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎያለፈነው፡፡የዚያመገለጫውም እልቂት፣ ግድያ፣ ጭፍጨፋና የማያባራ ጦርነት ነበር። ያንን ተከትሎ፣ ሰለባ ለኾኑት ዜጎች መታሰቢያ እንዲኾንና ያ-የግድያና የእልቂት ታሪክ እንዳይደገምና መማሪያ ይኾን ዘንድ መታሰቢያ ያስፈልጋል ብለው ባመኑ በጥቂት የ ትውልድ- በጎ ፈቃደኞች ጥረት የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማኅበር ሙዚየሙምተመሰረተ፡፡ ተቋቋመ እንደሌሎች ሀገሮች የቀድሞ ታሪክ በኢትዮጵያም በፖሊቲካ ልዩነት ምክንየት ተቃዋሚዎችን ማሰርና መግደል የተለመደ ቢኾንም፣ በተለይ የደርግ መንግሥት በዜጎች ላይ የፈጸመው ድርጊት የከፋና አሰቃቂ ነበር ፡፡ በተለይ ሕዝቡያመጣውንለውጥ፣ በመሳሪያ ትጥቅ ብዛትና ማንአለብኝነት፣ በኃይልና ጉልበት ስልጣኑን በሙሉ ተቆጣጥሮ፣ ተቃዋሚ እንዳላይ በሚል መርሕ የለውጥ ሐዋርያ የነበረውን ትውልድ በተደራጀና በተጠና አኳኋን በማሰር፣ በመግረፍ፣ በአደባባይ በመረሸንና በመጨፍጨፍ ያንን ሀገር ወዳድትውልድአጠፋ፡፡ በአንድ የታሪክ ወቅት ለተከፈለ መስዋዕትነት፣ ለተፈጸመ ጀብዱ መታሰቢያ ሐውልት ማቆምና ሙዚየሞችን መክፈት በዓለም
አቀፍ ደረጃ የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌም በእኛም ሀገር፣ በስድስት ኪሎ አደባባይ የቆመው የሰማዕታት መታሰቢያና በአቡነ ጴጥሮስ ስም ተሰይሞ የተሠራው ሐውልት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ እናም፣ በመስቀል አደባባይ ጫፍ ላይ ተገንብቶ ያለው የቀይ ሽብር ሰማዕታት ሙዚየም በደርግ ዘመን ለተጨፈጭፉት ዜጎች መታሰቢያነት ይኾን ዘንድና ለመጭው ትውልድ መማሪያ እንዲኾን “መቼም የትም እንዳይደገም!!” በሚል መሪ ቃል መንግሥት በሰጠው ቦታና ማኅበር የመመሥረት ፈቃድ ሊገነባ ቸሏል። ማኅበሩ ሲመሠረት እና ሙዚየሙ ሲገነባ የነበረው አንኳር ዓላማ የሚከተለው ነበር፥
እውነት አፈላላጊ ኮሚሽኖችን በማቋቋም ዜጎች ሳይሸማቀቁ የተፈጸመውን ግፍና ሰቆቃ ሃቁን እንዲያወጡና በታሪክም እንዲመዘ ገብ ማስቻል፡፡ አጥፊዎችን በሕግ እንዲጠየቁና የበደሉትን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ፡፡ የጥቃት ሰለባዎች ከደረሰባቸው ስቃይ እንዲያገግሙና የወደፊት ሕይወታቸው እንዲስተካከል ማድረግ ፡፡ በመጨረሻም “መቼም፣ የትም እንዳይደገም!!” የሚለውን የሙየዚየሙን መሪ ቃል በህትመት፣ በትምህርት ቤቶች ፣ እንዲሁም በተለያዩ የሕዝብ መገናኛ ብዙኀን በመጠቀም ያ ! ክፉ ቀን መቼም እንዳይመጣ፣ መጭውን ትውልድ የማስተማር፣ የማንቃትና የማዳን ሥራ መሥራት ነው፡፡ ማኅበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ ከላይ የተገለጹትን ቁልፍ ተልእኮዎችን ለመተግበር ታቅዶ በተወሰነ ደረጃ ተሳክቷል፡፡ ኾኖም በተለያዩ ምክንያቶች፣ በዋነኝነት በውስጥ የአመራር ችግር፣ በውጭ የተወሳሰቡ ተግዳሮቶች እንዲኹም በዓለም አቀፍ ደረጃ በነበረው የኮሮናና ሌሎች መሰል እንቅፋቶች የተነሳ የታቀደው ኹሉ አልተሳካም። ይኽን ክፍተት ለመሙላት፣ አዲሱ ቦርድ ማኅበሩን የማጠናከር ጥረት ቀዳሚ በማድረግ ዐቅሙን ለማጎለበት የውስጥ አደረጃጀቱን በሰለጠነ የሰው ኃይል እያጠናከረ ሲሆን፣ የሙዚየሙንና በውስጡ ያለውን መጻሕፍት ቤት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲኾን ተግቶ እየሠራ ነው፡፡ ከዚኽም በላይ፣ ማህበሩ ማሕበራዊ ግዴታውን ለመወጣት፣ አጋዥና ደጋፊ የሌላቸ ውን ሰለባዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በቅርብ እየተከታተለ ወርኃዊ የገንዘብ እርዳታ ማድረጉን ቀጥሎበታል፡፡ ይኽ ብቻ ሳይኾን፣ ማኅበሩ ተጠናክሮ በየክልሉ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ከፍቶ ለመንቀ ሳቀስ ራእይ ሰንቆ ይገኛል። ብሎም፣ የ-ያትውልድን ዓላማ፣ ጽናትና ድክመት ያኹኑ ትውልድ ሐቁንና ሃቁን ብቻ እንዲያውቅ ከሚመለከ ታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለወጣቶች ለማስተላለፍ ታቅዷል። ከዚኽም በላይ፣ በሀገር ደረጃ የገጠመንን የጦርነትና የግጭት ፈተና ለመሻገር በንግግር፣ በምክክር፣ በውይይትና  በሰላማዊ  መንገድ መፍትሔ ማፈላለግ አለብን ብሎ ማሕበራችን ያምናል። ስለዚኽ በዚኽ ዙሪያ ከሚሠሩ ሕጋዊ ተቋማትና ወገኖች ጋር ለመሥራትም አንዱ ራእያችን ነው። ይኽንን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የማኅበሩን የአምስት ዓመት የሥራ እቅድ ሰነድ አዘጋጅተን ወደ ሥራ ገብተናል፡፡ በመጨረሻም መጭውም ዓመት የሰላም፣ የእድገት፣ የዕርቅና የመመካከር ዘመን እንዲኾንልን በማኅበሩ ስም ምኞቴን እገልጻለኹ፡፡

ሲሳይ ክፍሌ

የቀይ ሽብር ምሣሌዎች

(ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ)

“ቀይ ሽብር” የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ጥቅም ላይ የዋለው በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ነው። ወቅቱ የቦልሼቪክ ኮሚኒስት ፓርቲ የዛሩን (ንጉሱን) ንግሥት በከተማ ዐመጽ አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ነው። የቀይ ሽብር መለያው ግድያ ብቻ አይደለም። መጠነ – ሰፊ እሥራት፣ አሰቃቂ ግርፋት፣ አካላዊና አእምሯዊ ጥቃት፣ ክሀገር ማሳደድንም ጠቃልላል። ቀይ ሽብር በዋነኝነት የሚካሄደው በመንግሥትና በደጋፊዎቹ ነው። በዓለም ላይ ቀይ ሽብር ከተካሄደባቸው ሀገራት መካከል ራሺያ፣ ካምቦዲያ፣ ኢንዶኔዥያና ኢትዮጵያ ተደጋግመው ጠቀሳሉ። ለጠቅላላ ዕውቀት በሚረዳ መልኩ በነዚህ ሀገራት የተካሄዱት የቀይ ሽብር ሂደቶችን (ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰቡትን) ልዩነትና ተመሳሳይነታችውን በግርድፉ እንይ።

  ሀገርራሺያኢትዮጵያ
  ውጤትየቦልሼቪክ መንግሥት መጠናከር፣ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ መፍጠር።የወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) መጠናከር፣ የብሔር ታጣቂዎች መነሳት።
ጭፍጨፋው የቆየበት ዓመት4   ዓመት2   ዓመት
የሟቾች ቁጥር (ግምት)ከ 100 ሺዎች እስክ 1 ሚሊየን ተኩል።ከ10 ሺ አስክ 500 ሺ።
ዋነኞቹ የጥቃቱ ሰለባዎችየንጉሣውያን ቤተሰቦችና ደጋፊዎች፣ ከበርቴዎች፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች (ሜንሼቪኮች)።ተቃዋሚ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ ተማሪዎችና ምሁራን።
ቀይ ሽብር አራማጆችሥልጣን የያዘው ቦልሼቪክ (ኮሚኒስት) ፓርቲና የስለላ ደርጅቱ (ቼካ)።ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ)፣ ደጋፊዎቹ ማርክሲስት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የቀበሌ ታጣቂዎች።
  ፍልስፍናኮሚኒስት (ማርክሲስት -ሌኒኒስት)።ማርክሲስት- ሌኒኒስት።
ሀገርካምቦዲያኢንዶኔዢያ
  ውጤትየሥርዓቱ መውደቅ።መንግሥታዊ አምባገነንነት መጠናከር።
ጭፍጨፋ ው የቆየበት ዓመት3 ዓመት1   ዓመት ተኩል
የሟቾች ቁጥር (ግምት)ከ1.5 ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን።ከ 200 ሺ እስከ 1 ሚሊዮን።
ዋነኞቹ የጥቃቱ ሰለባዎችምሁራን፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ አናሳ ብሔረሰቦች።ኮሚኒስቶች፣ ግራ ዘመም አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች፣ የቻይና ዝርያዎች።
ቀይ ሽብር አራማጆችየኬመር ሩዥ ወታደራዊ መንግሥት።የመንግሥት ወታደሮችና
  ፍልስፍናገጠር መር የቻይና ኮሚኒዝም (ማኦኢዝም)።ፀረ ኮሚኒስት።

የሀገረ እንግሊዝ እስር ቤት (ከ-120ዓመትበፊት)

ከ-የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአውሮጳና መካከለኛው ምሥራቅ [1903 ዓ፡ም]

ከኅሩይ ወልደ ሥላሴ

ዳራ፥1903 ዓም የእንግሊዝ መንግሥት ንጉስ ጆርጅ ሲነግሥ በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላችው ሀገራት መካከል ኢትዮጰያ አንዷ ነበረች። ለዚህም በራስ ካሳ የሚመራ ቡድን ወደዚያ አቅንቷል። ቡድኑ እግረመንገዱን ፈረንሳይና ጣሊያንንም እንዲጎበኝ ግብዣ ተደርጎለታል። ከልኡካን ቡድኑ መሃል አንዱ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ነበሩ። ይህ ጽሑፍ የየዕለቱን ዝርዝር ማስታወሻ ይወስዱ ከነበሩት ከኅሩይ ወልደ ሥላሴ ዘገባ ላይ የተቀነጨበ ነውመልካም ንባብ።

በዚያን ጊዜ የነበሩት እስረኞች 1 ሺ 500 ይኾናሉ። ለነዚኽ ኹሉ ለየብቻቸው አንዳንድ ጓዳ ሰጥተዋቸዋል። የሚተኙበት ፍራሹ፣ የሚበሉት ምግብ፣ የሚሞቁት እሳቱ እንደሚገባ ኾኖ ዘጋጅቶላቸዋል። ደግሞ ለሽንታቸውና ለዐይነምድራ ቸው ጥሩ ጥሩ ሳሃን አቅርበውላቸ ዋል።  ልብሳቸው ንጹሕ የታጠበ ነው። እግርና እጃቸው አይታሰርም። ቤቱን ግን በስተውጭ ይቆልፉባቸ ዋል። እንዳይጨልምባቸው በመስታ ወት የተገጠመ በስተውጭ የብረት ወም(ን)ፊት ያለው መስኮት አድርገ ውላቸዋል። ታሰረ መባሉ ከዘመዱ መለየቱ ብቻውን መቀመጡ ነው እንጂ ሌላ መከራ የለበትም።

ሹማምንቱ መጀመሪያ እስሩን [እስረኛውን] ሲቀበሉ ደብተር ያቀርቡና እርሱ በገዛ እጁ ስሙን፣ የታሰረበትን ቀኑን፣ ዓመተ ምሕረቱን፣ ለዚህ ያበቃውን ወንጀሉን ያጽፉታል። ክዚህ በኋላ የለበሰውን ልብስ አውልቀው አዲስ ልብስ ወይም የታጠበ ልብስ ያለብሱታል። አካላቱንም እንዲታጠብ ይነግሩታል። እንዲህም ማድረጋቸው በልብሱና በአካሉ እድፍ በሽታ ይዞ ገበቶ እንዳይሞት ወደ ሌሎች እስሮችም [እስረኞች] ደዌ እንዳያስተላልፍ ነው። ከዚኽ በኋላ በሚዛን ይመዝኑታል። ይህም ሰውነቱ በመብልም በሐዘንም እንዳይጎዳ ለማወቅ ነው። ወደ ስፍራውም ሲወስዱት የታሰረበትን ወንጀሉንና የሚፈታበትን ቀን ወሩንም ጽፈው በሚተኛበት ስፍራ በስተወጭ ከበሩ ላይ ይሰቅሉለታል። ሲወጣና ሲገባ ያንን እያየ በኃጢያቱ ያዝናል። የሚፈታበትንም ቀን ይቆጥራል። ሹማምንቱም ቀኑ እንዳያልፍባቸው ተጠንቅቀው ይጠብቃሉ። ይፈታ የተባለበት ቀን አትርፈው አንድ ቀን ቢያሳድሩት ሹማምንቱ ይቀጣሉ።

ደግሞ ያንዱን መንግሥት ሰው አንዱ መንግሥት የሚያስረው አይመስለንም ነበር። ነገር ግን የጀርመን መንግሥት ሰው በልብሱ ላይ የወታደርነት ምልክት ያለበት ታስሮ ዐየን። ደግሞ በመታሰሩ የተናደደ ሰው ድንገት ታንቆ ወይም በምድር ላይ ወድቆ፣ ወይም በግምብ ላይ ተጋጭቶ እንዳይሞት በሚታሰሩበት ቤት በላስቲክና በፍራሽ የተነፋ ለስላሳ ነገር ያለበት ነው።

ይህም ሁሉ ለሕዝባቸው መራራታቸውን ያስረዳል። ኣንኳን ድሀና ንጉሥ ቢሆን ለጊዜው የማይበድል የለም፣ ስለዚህ በደሉ በተገለጠበት ጊዜ ጥቂት ቀን እንዲቀጣ ማድረግ ነው እንጅ ቢሞት ምን ያጎድላል ብሎ በክፉ ስፍራ ማሰር መልካም አይመስለኝም።

ደግሞ እስረኞች ድንገት የታመሙ እንደሆነ፣ ሐኪሙ ከዚያ አውጥቶ፣ በመልካም ሆስፒታል አግብቶ፣ በንጹሕ ስፍራ አስተኝቶ፣ ንጹሕ ልብስ አልብሶ ያስታምማቸ ዋል። ሐኪሙ የእስረኞች ነው። ሆስፒታሉም እዚያው አጥር ግቢ ነው። ዳግመኛ ባንድ ስፍራ ስለተቀ መጡ ደዌ እንዳያገኛቸው ተብሎ መስክ የበቀለበት ልዩ ልዩ አበባ የተተከለበት ሰፊ ሜዳ አላቸው። ወደ ማታ እየመጡ ከዚያ ይናፈሳሉ።

መዐልቱንም ከፋፍለውላቸዋል። ለጫዋታ ጊዜ አላቸው፣ ለሥራም ጊዜ አላቸው፣ ለጸሎትም ጊዜ አላቸው፣ ለእረፍትም ጊዜ አላቸው። ከኹሉ ይልቅ እግዚአብሔርንና ሰውን እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርተውላቸዋል። በዚያው በወህኒው አጠገብ ከቅጥር ግቢ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸዋል። እሁድና በሌላ ቀን ወደዚያ እየሄዱ ቅዳሴ ይሰማሉ፣ ጸሎት ይጸልያሉ፣ ቁርባን ይቆርባሉ። አስቀድሞም በሠሩት ሥራ ንስሐ ይገባሉ።

ሰውን ተክፋቱ የሚመልሰው የመንግሥት ቅጣት ብቻ አይደለም። እነሆ በሀገራችን በኢትዮጵያ አንዳንድ ሌቦች እየተያዙ በ1 ዐራት እንዲከፍሉ ይፈረድባቸዋል። ይህንንም ለከፈሉ፣ ወዲህ ደግሞ እንደገና ሲሰርቁ ይያዙና ይገረፋሉ። ከተገረፉም በኋላ እንደገና ይሰርቁና እጃቸው ይቆረጣል። ነገር ግን በመጀመሪያ ሰርቀው በ1 አራት በከፈሉ ጊዜ መልካም መምህር ቢያገኛቸው፣ ሌቦች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም የሚለውን ቃል በገርነት ቢነግራቸው፣ እንኳን 2ኛ ሊሰርቁ እንዲያውም አያስቡትም ነበር። በዚህ ምክንያት እንኳን ከሥጋ ቅጣት ከነፍስም ቅጣት ይድኑ ነበር።

ከዚያ በኋላ ሥራ የሚሠሩበትን ቦታ ለማየት ሄድን። መጀመሪያ ኹሉም አንድነት የሚሰበሰብበት ወለል ነው። ሹሙ በዚያ ላይ ቆሞ አንድ ጊዜ ቢያፏጭ በሩን እየከፈተ ለቀቃቸው።   ኹለተኛ  ቢያፏጭ ሁሉም ቶሎ ብለው በየሥራቸው [የእስር ክፍል] ገቡ። አናጢውም፣ አንጥረኛወም፣ ሰፊውም፣ ስጋጃና ጆንያ የሚሠራውም፣ ብሩሽም ሌላም ዓይነት የሚሠሩ ሰዎች ኹሉ በየሥራቸው [የእስር ክፍል] ገቡ። እኛም ከፍ ባለ ስፍራ ቆመን እያየን የሥራውን ማማር፣ የሠራተኞቹን ፍጥነት እጅግ አደነቅን።

ደግሞ ባንድ ወገን የሥራ ተማሪ ቤት አለ። ሥራ የማያውቅ ሰው የታሰረ እንደሆን ወደዚያ እየገባ ይማራል። እስኪፈታ ድረስ በተማ ረው ሥራ ለመንግሥት ያገለግላል። ከተፈታም በኋል ታስሮ በተማረው ሥራ ገንዘብ አግኝቶ ጌታ ሆኖ ይኖራል። በእዳም ታስሮ እንደሆን በእስር ቤት ሆኖ ሥራ አግኝቶ እዳውን ይከፍላል። ጭራሽ ሥራ የማይገባው ፈዛዛ የሆነ እንደሆን ግን እስኪፈታ ድረስ ለመንገድ ድልድል የሚሆን ድንጋይ እየቀጠቀጠ ይቀመጣል። ደግሞ እስረኛው በታመመ ጊዜ ሐኪም በልዩ ልዩ መድኃኒት ካከመው በኋላ የማይድን ሆኖ የሞተ እንደሆነ ዘመድ ካለው ከዋና ሰው በቀር የቀረው ድሃው እዚያው በቅጥር ግቢ ይቀበራል። ደጃዝማች ካሳ ራሳቸው 36 መቃብር ቆጠሩ። ደግሞ እንደኛ አገር እንደ ኢትዮጵያ ደንብ መሠቀል የሚገባውን ሰው የሚሠቅሉበትን ስፍራ  ዐየን።   ጉድጓድ  ተቆፍሮ እንዲህም ማድረጋቸው ለእስረኞቹ መጥፎ ምግብ ይመግቡዋቸዋል ብለን እንዳንጠረጥር፣ የእስረኞቹን አለመጎዳት፣ የመንግሥታቸውንም ደግነት ለእኛ ለማስረዳት ነው።

በጉድጓዱ መካከል 4 መአዘን እንጨት አጋድመውበታል። በዚያ ገመድ (ሸምቀቆ) አስረውበት የወንጀለኛውን አንገት አርገው ቁልቁል ይወረውሩ ታል። ያን ጊዜውኑ ከመቅጽበተ-ዐይን ይሞታል። ይህንንም ካየን በኋላ ወደ ሌላ ስፍራ ወስደው እስረኞቹ ኹሉ የሚመገቡትን ምግብ አሳዩን። ዳቦው የጥቁር ስንዴ ከመሆኑ በቀር ኹሉም መልካም ነው። ጥቁርነቱም ላይን ነው እንጅ ጣእሙ ግን ይጣፍጣል። የጤና ምኒስትሩ ከኛ ጋር ነበሩና ዳቦውን አንስተው  ቀምሰው  አቀመሱን።

እኛም የእስረኛው ቤት እንዲህ ማማሩ፣ መንግሥቱም ለሕዝቡ እንዲህ አድርጎ ማዘኑን እያነሳን ስንጫወት ነጋድራስ አስቤ ምንም ቢሆን ስሙ እሥራት ነውና በዙፋኑም ቢያስቀምጡት ደስ ይለው አይመስለ ኝም አሉ። እኔም ይህስ እውነትዎን ነው። የሰው መጀመሪያ ሕይወቱ ሚስቱ ናት፣ 2ኛ ልጆቹ፣ 3ኛ ልጆቹ [የልጅ ልጆች] ናቸው። ከሚስቱ ከልጆቹ ከተለየ ምን ሕይወት ይባላል ብዬ መለስኩላቸው።

ከድር-የከርቸሌው ኪስ አውላቂ

(በፋሲካ መለሰ ከተጻፈው <ከኒያ ልጆች ጋር> ከሚለው መጽሐፍ የተውሰደ)

ከድር በ-1970ዎቹ ውስጥ በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት የታወቀ ወመኔ ነበር፡፡ በስርቆትና በኪስ አውላቂነት ነው ታስሮ በተደጋጋሚ የሚመጣው፡፡ቢያንስ ሦስት ዐራቴ ተመላልሷል፡፡የሚገርመው እሥር ቤትም ኪስ ያወልቅ ነበር፡፡ መቼስ ከርቸሌ የአንድ ከተማ ያህል ሰው የሚኖርበት አይደል ኪስ ለማውለቅ በጣም የሚመቸው እሁድ በዘመድ ጥየቃ ሰዓት ነው፡፡ እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚያነጋግሩት በጣም ተጠጋግተውና ተፋፍገው ስለሆነ ለነከድር በጣም ይመቻል፡፡

እነ ከድር እስረኞች ከዘመድ ገንዘብ ሲቀበሉ ያያሉ፤ የትኛው ኪሱ እንደሚከቱም ያውቃሉ፡፡ እናም እስረኞች ገና ተቀብልው ኪሳቸው ውስጥ ሲያስገቡ ላጥ ያደርጉዋቸዋል፤ ወይም ወደ ክፍላቸው በመሄድ ላይ እያሉ ትኩረታቸውን በማስቀየስ ይልፏቸ ዋል፡፡  አብዛኛውን ጊዜ የሚሰረቋቸው የደረቅ ወንጀለኞችንና የገጠር  እስረኞችን  ነው፡፡  የኛ ልጆች ‘የፖለቲካ እስረኞች’ ተሰርቀ ናል ሲሉ ሰምቼ አላውቅም፡፡ አንዴ እንዲኽ ሆነ፡፡ የመንዝና ግሼው ጓደኛዬ ሽፈራው ደምሴ ‘አኹንም በሕይውት አለ’፣ አቶ ደስታ የሚባሉ ጓደኛ ነበሩት፡፡ ኹለቱም የሚኖሩት ቀጠሮ ዘጠነኛ ቤት ነበር፡፡ አንድ እሁድ ቀን ከድር ሞጭላፋው አቶ ደስታ ከጠያቂዎቻቸው ገንዘብ ተቀብለውና ተሰናብተው ሲመለሱ ፊትለፊት ያገኛቸዋል፡፡ ከዚያም በድንገት እንትናቸውን ጨብጦ አንተ ነኽ በዚኽ እንትንኽ ሚስቴን እንዲኽ ያደረካት ይላቸዋል፡፡ አቶ ደስታ፣ በጣም ደንግጠው በመከራ እንትናቸውን አስለቅቀው ወደ እስር ክፍላቸው በፍጥነት ይገባሉ፡፡

ትንሽ ቆይተው ኪሳቸውን ቢዳብሱ ገንዘባቸው የለም፡፡ እንዲሁ እርር ድብን እንዳሉ ጉዳዩን ለጓደኛቸው ለሽፈራው ያጫውቱታል፡፡ሽፈራው ደምሴ ለጓደኛ ሙት ነው፤ እናም አንድ ዘዴ ፈጠሮ አማከራቸው፡፡ አቶ ደስታም ተስማሙ፡፡ ከድር ለሙጭለፋ በየእስር ክልሉና በየክፍሉ እንደሚዞር ያውቃሉ፡፡ ከዚያም ዘጠኝ ቁጥር እነሱ ክፍል እስኪመጣ ሲጠብቁት ከረሙ። አንድ ክፉ ቀን ከድር መጣ፣ ቤቱን ገለማምጦ የሚሰረቅ ሲያጣ፣ ወደ ሽንት ቤት አልፎ ሄደ፡፡ ሽፌና አቶ ደስታ ደብቀው ያስቀመጡትን የፍልጥ እንጨት ከፍራሽ ሥር ያወጡና ተከታትለውት ገቡ፡፡ ከድር ሽንቱን እየሸና እያለ ሽፈራው ሽንጡ ላይ ደህና አድርጐ ይመታዋል፤ መልሶም ይደግመዋል፡፡

አቶ ደስታ ደግሞ ያንን ኪስ አውላቂ እጁን እያከታተሉ ይቀጠቅጡታል፡፡ ከድር የመከላከያ ዐቅሙ ወደ ዜሮ ይወርዳል፡፡ ከዚያ በኃላ ያለውን ውርጅብኝ መገመት ነው፡፡e ጩኸት ተበራከተ፤ ካቦ የሚባሉት ራሳቸው እስረኛ የኾኑ የእስረኛ አለቃዎች መጡ፣ ቀሪው እስረኛም ለወሬ ተንጋጋ። ከድር ሽንት ቤት ውስጥ ተዘርሯል፡፡ በወህኒ ቤት ሕግና ሥርዓት መሠረት ደብዳቢና ተደብዳቢ የእስር ቤት አስተዳደር ፖሊሶች ዘንድ ይቀርባሉ። ምርመራው ቀጠለ፡፡

መርማሪ፡ ለምን ደበደባችሁት

እነሽፈራው፡ ከሚኖርበት ክልል፣ ከዓለም በቃኝ ክልል አልፎ መጥቶ እኛ ክፍል ሲሰርቅ አገኘነው፤ ሸሽቶ ሽንት ቤት ሲገባ ተከታተለነው፤ ሊመታን ሲፈልግ ራሳችንን ተከላከልን፡፡

መርማሪ፡ አንተ ያለኸው ዓለምበቃኝ፤ ምን ልትሠራ ቀጠሮ ዘጠነኛ ቤት ያውም ሽንት ቤታቸው ወስጥ ገባኽ

ከድር፡ ሽንቴ መጥቶ ልሸና መርማሪ፡ ‹ዓለም በቃኝ ሽንትቤት አለ አይደል?›

ከድር፡ ‹በዘጠነኛ ቤት በኩል ሳልፍ ሽንቴ ስለመጣ ነው›

መርማሪ፡ ‹ነው እንዴ? አንተ ተመላላሽ ሌባ! አናውቅህም፣ የውጭው አልበቃኽ ብሎ ጊቢ ውስጥ እንደምትመነትፍ እናውቃለን> ካለ በኋላ፣ <በል ይኼን ሌባ ወስደህ በካቴና እሰርልኝ› በማለት የጠበቃ ፖሊሱ አዘዘ፡፡ ድራማው ተጠናቀቀ፣ ውሳኔውም ተግባራዊ ኾነ።

ሌላ ጊዜ ሽፈራውና ከድር እዚው ግቢ ይገናኛሉ፡፡ ከድር ‹ሥራ› ላይነበር፡፡ ሽፈራው አፍጥጦ ዐየው፡፡ ከድርም የተቅለሰለሰ ‹እናንተ መንዜዎች አትድረሱብኝ፤ አልደርስባች ሁም፤ ሥራዬን ልሥራበት› ዓይነት ንግግር አድርጎ አለፈ፡፡

ከታሪክ ማኅደር

(በአፈወርቅ ከተማ የተሰበሰበ)

ተዋበች( ሕይወት ተፈራ እንደ ጻፈችው)

አያትህ ታላቁ ኢያሱ ለትምህርት ብዙ ዋጋ የሚሰጡ ሰው ነበሩ..” አለችው ተዋበች ለልጆ ” ዐውቃለሁ፡፡ አንቺም ነገርሽ ሁሉ እንደሳቸው ነው፡፡ ” ስለ ትምህርት ላወራህ ፈልጌ ነው የሳቸውን ስም ያነሳሁ” “በሳቸው ዘመን የተማሮች.. ቁጥር ብዙ ነበር ይላሉ፡፡ ስንክሳርም በብዛት የተጣፈው በሳቸው ግዝየ ነው፡፡ አለች “እኔም ስለሱ ነግርሻለሁ እያልሁ ነበር፡፡ ሌላ ደግሞ ባለፈው ኻረብኛ ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ እንዲመለስ ፈልጋለሁ ስትይ-ማል ነበር?

“ትርጉም አዎ…አዎ ስል ነበር፡፡ ባለፈው መላከ ጠሐይሮብዓም ትርጉም ላይ ቢበረታ ብያቸው ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ሚመልሱ ሰዎች አምጥተው ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡ ለእነመላከ ጠሐይ ሃይማኖትን የሚያስተምረውንና ላገር የሚጠቅመውን ሁሉ እንዲያስተረጉሙ ነግሪያቸው እነሱተመካክረው  ወስነዋል፡፡  ምንትዋብ ገጽ(202)።

ሀገር እንዲህ ከትውልድ ትውልድ በእውቀት እና በመረጃ እየተገነባ የዘለቀው፣ በቅብብሎሽ ነው!!! እና ትውልድ ለሞራሉ ሃይማኖቱን፣ ለዕውቀቱ ስንክሳር እና ትርጉም እየመገቡ ለሺ ዓመታት የዘለቀ የማንነትን፣ አጥፍቶ፣ የበታችነት እና ባርነትን ሊጭን የመጣ ጠላት ሁሉ፣ በየጊዜው ያደረገው የታሪክ ማኅደርን በማጥፉት ነው!!!

ከዙላ እስከ መቅደላ(የተጓዘው አሜሪካዊጋዜጠኛእንደጻፈው)

እነዚህ ጥቁር ኮት የለበሱ አዋቂ ሰዎች ለስሙ” ፊላንትሮፒስት ተባዬዎች” ሁሉም ባይሆኑ አብዛኛቹ እስረኞች (የቴድሮስ ምርኮኞች) ከመለቀቃቸው በፊት ብዛት ያለውን የተዘረፈ ንብረት በእጃቸው አድርገው ነበር፡ (ገጽ 218)፡፡ እንዲሁም የኑጉሳዊ ብራና ጽሑፎች ክምር፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የፎቶ አልበሞች በአማርኛ የተጻፉ መጽሐፍ ቅዱሶች  የጸሎት  መጻፍቶች…  በሺ የሚቆጠሩ እነዚህ ዕቃዎች በየቦታው ግራ በሚያጋባ ሁኔታ፣ በአለታማው አምባ፣ በዳገቱና በኮረብታዎች ወደ ካምፕ (የእንግሊዝ ጦር) በሚወስደው የሁለት ማይሎች ርቀት ባለው ቦታ ሁሉ ተንጠባጥበው እስኪገኙ ድረስ ተበትነዋል፡፡ (ገጽ 286)
ነበር እንዳይረሳ (ደጃዝማች ከበደ ተሰማ እንደጻፉት)
የዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ጸሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ የተጻፈውን እንደዛሬው ጊዜ ማተሚያ ቤት ሳይኖር በብራና በእጅ ጽሕፈት ተዘጋጅቶ ለትውልድ
እንዲተላለፍ በቤተ ሥና፣ በታላላቅ አድባራትና በገዳማት ተቀምጦ የነበረውን
በቤተ-ሥ ተቀምጦ የነበረውን ጠላት (ፉሺስት) ኢትዩጵያን በወረራት ጊዜ ሲያጠፉና ሲበትን፣ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ስለወገኖቻቸው የተተረከው ደስ ስላላ ቸው (ባንዳ) ታሪኩ በሙላ እንዲጠፉ በማሰብ እናንበው በማለት እየተዋሱ በመውሰድ ጠፉብን እያሉ በነሱ ጠባብ አስተያየት ከተቀመጠበት ገዳም እንደወጣ አጥፈተውት ቀርቷል፡፡ (ገጽ 15)

ከቤተመንግ ሥት ዶሴ (አስናኝመኩሪያ መካሻ እንደ ጻፈው)

ይኽ በብላቴ ጌታ ወልደማሪያም አየለ ከ1912 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1925 ዓ.ም የተጻፈ የታሪክ መዘክር ጠቃሚ የሆኑ የቀድሞ ታሪካችንን የሚያቀርብ ነው፡፡ …በእጄ ሊገባ የቻለው … በግንቦት 1983 ዓ.ም የደርግ ሥርዓት ወድቆ ኢሕአደግ ሀገሪቱን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት መንግሥታዊ ሰነዶች ከተቀመጡበት እየወጡ ሲበተኑና ስለሚቸበቸቡ መጽሐፍትና ማስታወ ሻዎችን ከጎዳና ላይ የመጽሐፍት ሻጮች ማግኝት የተለመደ እንደ ነበር ይታወሳል (ገጽ 8)፡፡ ይኸው ዛሬም በዲጅታል ዓለም ታሪክ በማዛባት ሀገር የሚፈርሰው ቅድሚያ መረጃና ሰነድን በማጥፋት ነው!!! “የሰው አገሩ ምግባሩ ነው” ይባል የለ‼ የሰው ምግባሩ ታሪኩ ነው! ታሪኩም ማንነቱ ነው! የትውልድ ታሪክ ጠብቀን፣ በበጎ ምግባር ትውልድ ካልገነባን አገር እንንዳለን!

አሊኹሴንና የኢትዮጵያ አፈር

ዳራ፥-አሊ ኹሴን የቀድሞ የኢሕአፓ አባል ሲኾን፣ ከእስር ቤት ከተፈታ በኋላ ከሀገር ወጥቷል። በአኹኑ ወቅት በሀገረ ካናዳ የሚኖር ሲሆን፣ ለስደተኛና ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ወደር የሌለው ድጋፍ በማድረግ ይታወቃል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ከአርትስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። እነኾ!

ጋዜጠኛ፦ እንግዲኽ የሆድ ሆዳችንን እየተጫወትን ስለኾነ ነው በደንብ ላደምጥህ የፈለግኹት። ካንተ ውስጥ እንዲወጣ ስለሚያስፈልግ፣ እኛም ምናልባት ከሕይወትህ፣ ከመስዋዕትነትኽ… አንተ ስል፣ ልክ አንተን የመሰሉ በሕይወት ያሉ ስለሚያዩ፣ ስለሚያደምጡ ነውና እናንተ ከከፈላችሁት ብዙ መሥዋዕትነት የምንማረው ብዙ ነገረ ስላለ ነው፣ በደንብ እንድናወራ የፈለግኹት።

አሊ ሁሴን፥ እኔም ደስ ይለኛል።

ጋዜጠኛ፦ ምናልባት ማልቀሳችን ሊበዛ ይችላል፣ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም፣ በእንባ የሚወጣ ከሆነ።

አሊ ሁሴን፥– ልቆጣጠረው አልችልም።

ጋዜጠኛ፥– እውነት ነው። እንግዲህ ይቺ የምትወዳት ኢትዮጵያ፣ ዋጋ የከፈልክባት ኢትዮጰያ ከ40 ዓመታት በኋላ።

አሊ ሁሴን፥ 43 ዓመታት በኋላ…

ጋዜጠኛ፥አዎ፣ ከ 43 ዓመታት በኋላ…እና ከቤትህ ብፌ ውስጥ፣ ያየኋት የተከደነች ሳህን አለች። እዚች ሳህን ላይ የተጻፈ መልእክት አለ። ሳህኑ ውስጥ የተቀመጠው ከኢትዮጵያ ያስመጣኸው የኢትዮጵያ አፈር ነው። መልእክቱን ላንብበው፦

ይድረስ ለመላው ቤተሰቦቼና ቀባሪዎቼ፣ መጋቢት 13/1984 ዓ/ም።

ይድረስ ለመላው ቤተሰቦቼና ቀባሪዎቼ፣ የተፈጥሮ ሕግ ነውና ማንኛችንም የምንኖረው የተወሰነ ጊዜ መሆኑ ዕውቅ ነው። አጋጣሚ ሆኖ የምንሞትበትንና ቀንና ቦታ የማወቅ ዕድሉ ስለሌለን በሕይወት ባለንበት ጊዜ የምንመኘውን ሁሉ የማግኘት ዕድላችን ውሱን ነው። ስለሆነም ነገሮች ተስተካክለው በትግል ወቅት ላጣናቸው ሁሉ፡የክብር ቦታ ሰጥተን እኛም ወደማይቀረው የመጨረሻ ቤት ስንሄድ፣ ካለፍን በኋላ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ የምንመኘውን እንዲያደርግልን ኑዛዜ እንሰጣለን (ኣሟሟታችን በአደጋ ካልሆነ)። በዚሁ መሠረት፣ እኔ ከምወዳት ብቸኛዋ ሀገሬ ኢትዮጵያ ውጪ ሕይወቴ ቢያልፍ፣ የመቀበሩ እድል እስካለኝ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ወዳጆቼ የሚያመጡልኝን አፈር አጠራቅሜ ያስቀመጥኩት ለእናት ኢትዮጰያ ላለኝ ክብር፣ ፍቅር፣ ለመላው አካሌ ባይበቃም፣ ፊቴ ላይ በደንብ ተነስንሶ አንድም ሳይቀነስብኝ፣ እንድቀበር እና ቃሌ ሳይጣስብኝ ኑዛዜዬ ይፈጸምልኝ።

ከዊኒፔግካናዳ፡ መጋቢት 13/1992

ጋዜጠኛ፥– አፈሩን ነስንሱብኝ ብለኽ ተናዘሃል። የሚሰጥኽ ስሜት እስከ ምን ድረስ ነው?

ጋዜጠኛ፥– ደስ ነው የሚለኝ፣ ለምንድን ነው ይኼን ያልኩት… የሚገርም ነው… ምናልባት ሀገር ከመውደድ… እኔ ብቻ ኣይደለሁም፣ ብዙ ሰው ሀገሩን ይወዳል። እኔ የተለየኹ አይደለኹም። ልብስ እናምጣልኽ፣ እንደዚህ እናምጣልኽ ሲሉ ኹለት ነገሮች የተሟሉልኝ ይመስለኛል። እኔ የእስልምና ተከታይ ነኝ። ሙስሊም በመኾኔ በጣም ደስ ይለኛል። ያደኩት ደሞ በቄስ ትምህርት ቤት ነው። ዳዊት ደግሜ ነው ያደኩት። ልጅነቴን፣ እንዲኽ በቋንቋ እንድሠለጥን እንድማር ያደረገኝ፣ የቄስ ተማሪ በመኾኔ ነው።

በመጀመሪያ አንድ ሰው ምን ላምጣልኽ ብሎ ሲጠይቀኝ፣ ዳዊቴን አምጣልኝ ነው ያልኩት። ከዛ ውጭ ሰዎች ልብስ እናምጣልኽ ሲሉኝ፣ እሷን ነው [ኢትዮጵያ] የሚናፍቀኝ። እንደወጣኹ ብቀር የናቴን [ኢትዮጵያ] አፈር ሳልለብስ፣ በፈረንጅ አፈር እንዳልቀበር ነው። አፈር አፈር ነው ይላሉ ሰዎች። ግን አይደለም።

በጣም የማከብራት ወ/ሮ ቀለሟ ጥያቄ ጠየቅችኝ። ‘ብዙ ነገሮችን ስታደርግ ዐይቼሃለሁ፣ ከሀገር ቤት ምን ላምጣልኽ አለችኝ?”። “የምታመ ጭልኝ ከኾነ የናት ሀገሬን አፈር” አልኳት።  “አይ  አፈር  ላመጣልኽ ነበረና ካፈሩ ላይ እንደ ስኳር አንድ ማንኪያ አውጥቼ፣ በጥብጬ ጠጣኹትና አገሳኝ። ኩላሊት ነበረብኝ፣ የዚያን ቀን ነው መሰለኝ ጤናዬ የተመለሰው።

ምንጭ Arts TV World. https://www.youtube.com/watch?v=Y9rjmER4Pwc&t=250s

ልዩ ልዩ

ባህላዊው የኢትዮጵያ የሴቶች ቀን

ዓለም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን

መገለል ተከትሎ ከ-1913 ዓም ጀምሮ በወርኃ የካቲት 8 (ማርች 8) በዓለም ደረጃ (ሀገራችንን ጨምሮ) ይከበራል። ታዲያ ኢትዮጵያ የራሷ የሴቶች ቀን እያላት ለምን ማርች 8ን ታከብራለች? ከረጅም ዓመታት በፊት ጀምሮ በሶዶ ጉራጌ ሴቶች በአንድነት እና በፍቅር ተሰባስበው እናትና እኅቶችን የሚያሳርፉበት የሚንከባከቡ በት የሴቶች የክብር ቀን አላቸው።

ታዲያ ይኼንን ስንቶቻችን ዕናዉቅ ይሆን ? መርምረን የደረስንባቸዉን ሀገር በቀል በዓላት፣ ባህል እና ሥርዓት በጎነታቸውን እየመዘንን ለዓለም ማስተዋወቅ አይገባም ትላላችኹ? በሶዶ ጉራጌ “ወልቀነ” ማለት በየዓመቱ የመስቀል በዓል ከመከበሩ ሦስት ቀናት በፊት ዓመቱን  ሙሉ  በትጋት  ቤቷንና ቤተሰቧን የምታገለግለው የሶዶ ጉራጌ ሴት ክብር የምታገኝበት የዕረፍት ቀኗ ነው። በወልቀነ (በሴቶች ቀን) ሴት ልጅ ለብሳ አጊጣ ትነግሣለች፣ ስለክብሯ ጸጉሯን ያማረ ቅቤ ቀብታ፣ የጎመን ክትፎ መዐድ ተሰይማ ትበላለች፣ ትጠጣለች። “ወል ቀነ” ን (የሴቶች ቀን) ማክበር ሴት እናት፣ ሴት እኅት፣ ሴት ሚስትና ሴት ልጅ ማከበር ነው።

ይህ የቀደመ አኩሪ ሀገር በቀል ባሀል ከትውልድ ትውልድ ይሻገር ዘንድ ትጉኽ ሴቶች በአዲስ አበባ ማክበር ከጀመሩ እነኾ ዐራት ዓመት ኾኗቸዋል። በዚህ ቀን ድል ያለ ድግስ ተደግሦ ሴቶች ነግሰው ተከብረው ይውላሉ።  ዝግጅቱ ደንጌሳ ወይም ክትፎ የመብላት ጉዳይ አይደለም። የሴትን ልጅ ክብር የምናሳይበት እና ባህልን የማጉላት የማስተዋወቅ ጉዳይ እንጅ ….

ግጥም

ዴንጋሽ የጋደቢ         ከዛም ተረኛ ነኝ፣ ከብቶችን ለማገድ፡፡

Wrong Move

የኢሕአፓው ተስፋዬ ደበሳይ የደርግ ወታደሮችን ሸሽቶ አንድ ዶክተር ጓደኛው ቤት ኅቡዕ ገብቶ (ተደብቆ) እየኖረ ነው። አንድ ቀን ተስፋዬ ለዶክተሩ ጓደኛው፣ ቄስ አጎቱ ከገጠር ሊጠይቁት እንደሚመጡ ይነግረዋል። ጓደኛውም በሐሳቡ ይስማማ እና ቄሱ ወደ ቤታቸው ተስፋዬን ለማየት ይቀላቀላሉ። የተስፋዬ ደበሳይ አጎት ጠዋት እና ማታ ዳዊት ከመድገም እና ለማዕድ ሲቀርቡ ቆርሶ ባርኮ ከመስጠት ውጪ ብዙ የማይናገሩ ዝምተኛ ቄስ ነበሩ።  ሲያወሩ የንግግር ዘዬያቸው የሚያምር የባላገር ዓይነት ነው። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ቀናት ይቆያሉ። ተስፋዬም አጎቱን እያጫወተ መጽሐፍ እያነበበ እና ከጓደኛው ጋር ቼዝ እየተጫወተ ጊዜውን ያሳልፋል።

አንድ ቀን ምሽት ላይ እንደተለመደው ተስፋዬ ደበሳይ እና ዶክተሩ ቼዝ እየተጫወቱ ሳለ ቄሱ ዝም ብለው ይመለከታሉ። ጨዋታውም እየተጋጋለ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ይደርሳል። ዶክተሩ ተስፋዬን ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሷል። ተስፋዬም ላለመሸነፍ በከፍተኛ ኹኔታ ተመስጦ ያሰላስላል። ቄሱም እንደተጫዋቾቹ ተመስጠው ቼዙ ላይ አፍጥጠዋል። እንዴት ቢሄድ ከመሸነፍ እንደሚድን ሲያብሰለስል የነበረው ተስፋዬም  አንዱን የቼዝ ፈረስ በዘፈቀደ አንስቶ ያንቀሳቅሳል። ይኼኔ በተመስጦ ሲያዩ ከነበሩት የባላገር ቄስ አፍ አንድ ቃል ይወጣል “wrong move”።

ተስፋዬ እና ዶክተሩ በከፍተኛ ድንጋጤ ወደ ባላገሩ ቄስ ይዞራሉ። ቄሱም ደንግጠው መልሰው ያፈጣሉ። እኚያ ቄስ ትክክለኛ ቄስ ሳይሆኑ የኢሕአፓው ታጋይ የነበረው ሊቁ ጸጋዬ ገብረመድኅን (ደብተራው) ነበር። ተስፋዬ የትግል አጋሩን ዶክተር፣ ጓደኛው ቤት ለመደበቅ ከደብተራው ጋር ተመካክረው ያወጡት ዕቅድ ነበር።

(ከክብሩ ክፍሌ የቴሌግራም ገጽ የተወሰደ)

የቀይ ሽብር ሦስት የጽልመት ምዕራፎች

(ከ-ሬኔ ለፎርት “Ethiopia: An Heretical Revolution?” መጽሐፍ ላይ የተወሰደ)

ጽልመት ምዕራፍ አንድ

የመጀመሪያው የቀይ ሽብር ምዕራፍ በ-1969 ዓም በመስከረም ወር በኢሕአፓ አባላት ላይ ግድያ ተጀመረ። በዚያው ዓመት ጥቅምት 21 የኢሕአፓ ሰዎች ተረሸኑ፣ በሕዳር 18 ደሞ 17 እንደተገደሉ ተገለጸ። ይኹንም በዚያው ዓመት በጥር ወር 1969 የጄኔራል ተፈሪ ባንቴን ግድያ ተከትሎ ቀይ ሸብር በግላጭ ታወጀ። በሚያዝያ 9 መንግሥቱ ኃይለ ማርያም <የአብዮቱን ጠላቶች> ለመደምሰስ ለሕዝቡ ይፋዊ ጥሪ አደረገ። በየካቲት 26/1977 ዓም 40 እስረኞች ከአዲስ አበባ ውጭ ተወስደው ተረሸኑ። ሚያዚያ 21 ቀን 1968 ዓ/ም በተጠራ የመንግሥት ድጋፍ ሰልፍ ላይ የኢሕአፓን ወረቀት በትናችኋል የተባሉ ቁጥራቸው ያልታወቀ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

በመጋቢት ወር 1969 ለሦስት ቀን በተካሄደ የቤት ለቤት አሠሣ አንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ታሰሩ። የሜይ ዴይ በዓል አስመል ክቶ ክሚያዚያ 23/1969 ምሽት ኢሕአፓ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጥቃት ለማድረስ፣ ከገጠር አካባቢ የተሰባሰቡ ታጣቂዎች በከተማ ክሚገኙ መሰል ቡድኖች ጋር በመሆን ተጠርጣሪ የኢሕአፓ አባላትን መጨፍጨፍ ጀመሩ። የሟቾች ቁጥር 2000 ይደርሳል የሚሉ አሉ። በመንግሥት ይፋዊ መግለጫ ግምት ግን 732 ሰዎች በተክታዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ተገድለዋል። በግንቦት መጀመሪያ ቀናት የቀን ሰዓት እላፊ ታውጆ ቤት ለቤት አሠሣ ተካሂዶ ስዎች ታሰሩ። በግንቦት ወር የሴቭ ዘ ችልድረን ሴክሬታሪ ጄኔራል እንደገ ለጹት “1000 ወጣቶች (ሕጻናት) ተገድለው፣ ሬሳቸው አስፋልት ላይ ተጥሎ፣ በጅብ ተበልተዋል”።

እንደ ባለሥልጣኑ ግምት፣ ከ-100 እስከ 150 የሚሆኑ ወጣቶች (ዕድሜያቸው 12 የሚሆን ጨምሮ) በያንዳንዱ ምሸት ይገደሉ ነበር። በሰኔ 4 ምሽት ለሰኔ 5 አጥቢያ፣ 400 ተማሪዎች ተገድለዋል።  በመጀመሪያው የቀይ ሽብር ምዕራፍ ቢያንስ 2,500 ያህል ሰዎች አልቀዋል። በመንገድ ዳር የተጣሉ የሟች ዘመዶችና ጓደኞች ሐዘን መቀመጥ ተከልክለዋል። በመንገድ ላይ የተጣሉትን ሬሳዎችን ለመለየት ሙከራ የሚያደርጉ የቅርብ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውንም ለግድያ ወይም ለእስር ያጋልጣሉ።

በሌላ ገጽታ ደሞ አስከሬን እንዲወስዱ የተፈቀደላቸው ቤተሰቦች ሟች ለተገደለበት ጥይት እንዲከፍሉ ይጠየቁ ነበር። በኢሕአፓ ደጋፊነት ተጠርጥረው ለጅምላ እስር ከተዳረጉት አብዛኞቹ ለአሰቃቂ ስቃይ ይዳረጋሉ፡ ብዙዎችም ከተወሰነ እሥራት በኋላ የደረሱብት ይጠፋል። የእስረኛ ቤተሰቦች ምግብና ልብስ ማቀበል ይችላሉ፣ ወደሌላ አስር ቤት ከተዛወሩም ይነገራቸዋል። በተጨማ ሪም ቤተሰብ የእስረኞቹን መገደል የሚያውቀው፣  ለታሳሪው  ስንቅ ማምጣት እንደሌለባቸው በእስር ቤቱ ጥበቃዎች ሲነገራቸው ነው። አንዳንዴ፣ እስረኛው ተገድሎም ስንቅ በመቀበል ቤተሰብን ያታልላሉ። ጸሐፊው ሬኔ ለፎርት ስለታሳሪዎች ሁኔታ ሲገልጽ ቃል በቃል እንዲህ ይላል፡-

”አንድ ሰው ፀረ አብዮት ነው ተብሎ ለመጠርጠር የሚያስፈልገው መመዘኛ መሃይም አለመሆኑና እድሜው 20 ወይም ከዚያ ያነሰ መሆኑ ብቻ ነው፣ ባለሥልጣናቱ እድሜያቸው ከ 8 እስከ 12 የሚሆኑ ሕጻናትን የማሰር ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።”

ጽልመት ምዕራፍ ኹለት

ኢሕአፓ በዋነኝነት የተመታው በመጀመሪያው የጽልመት ምዕራፍ ቢሆንም ጭፍጨፋው ቀጥሏል። በርግጥ በዚኽ ኹለተኛ ምዕራፍ ዋነኛው ተጠቂ ኢሕአፓ ቢኾንም፣ ደርግ ፊቱን ያዞረባቸው የቀድሞ ደጋፊዎቹን ነበር። የመኢሶኑ መሪ እና የመንግሥቱ ኃይለማርያም የአይዲኦ ሎጂ አማካሪ የነበረው ኃይሌ ፊዳ በነሐሴ 1969 ታሰረ። ያን ተከትሎ በርካታ የመኢሶን ካድሬዎች ለእስር ተዳረጉ። ኃይሌ ፊዳም ከበርካታ ወራት አስር በኋላ ተገደለ። በዚያ ኹለተኛ የፍጅት ምዕራፍ ከ 3000- 4000 ሰዎች ተገድለዋል።

ጽልመት ምዕራፍ ሦስት

ሦስተኛው የጽልመት ምዕራፍ የተከናወነው በ-1970 ነው። በታኅሣሥ አጋማሸ ምሽት 300 ሰዎች ተገደሉ። እንደገና በታኅሣሥ መጨረሻ መስጊድ ውስጥ ጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎች በመንግሥት ታጣቂዎች ተጨፈጨፉ። አንድ ኢትዮጵያዊ እንደተናገረው፣ በዚያ ምዕራፍ በያንዳንዱ ቀን ከ25 እስከ 30 ሰው ይገደል ነበር። በዚያው ዓመት መጨረሻ፣ ዓለማቀፉ የሰብአዊ ተቋም አንደዘገበው፣ በ291 ቀበሌዎችና በዋናው እስር ቤት ወደ 30,000 እስረኞች ነበሩ። ይህ ቁጥር በየክፍለሀገሩ የታሰሩትን ሰዎች ስለማያጠቃልል፣ ግምቱ አናሳ ነው ማለት ይቻላል። የሦስተኛው ምዕራፍ ግድያ የተከናወነው በእስር ቤቶች ሲሆን በመገናኛ ብዙኃን ብዙም አይገለጽም ነበር።

የሐዘን መግለጫ

አርታኢ፡- ፋሲካ መለሰ ተባባሪዎች፡-

ደራሲ፦ ኃይለመለኮት መዋዕል እና ዮሐንስ አፈወርቅ

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top